News

Latest News

1

First News

በአዲስ አበባ አስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 74/2011 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 8 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 23 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ውስጥ የክ/ከተማው አስተዳደር ዋና የህግ አማካሪና ሕጋዊ ወኪል በመሆን በየትኛውም የዳኝነት እርከን በመቅረብ የፍትሕብሔር ክርክር በማድረግ የከተማ ነዋሪዉንና የአስተዳደሩን መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ፤ ይህን ሲተገብር የሲቪል ማህበረሰብና የነዋሪዉን ተሳትፎ ለማጎልበት የተለያዩ አደረጃጀትና አሰራሮችን ይተገብራል፡፡

2

Second News

በአዋጁ ከተሰጡት ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት የነዋሪዉን ንቃተ ህግ ማሳደግ፣የተለያዩ አስተዳደሩ የሚያደርጋቸዉን አስተዳደራዊ ዉሎች የማዘጋጀት፣ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀት፤ ሰብዓዊ መብትን ከማክበርና ከማስከበር አንፃር የፌደራሉን የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር መሰረት በማድረግ የከተማዉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማዘጋጀት መተግበርና በማስተገበር፤በከተማዋ የህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣዉን አዋጅ ለማስፈፀም የማስተባበር ሥልጣንና ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡